Friday, September 19, 2014

ጫልቱ አሳታሚ


“የጀሚላ እናት” የመፅሃፍ  ምረቃ ጥቅምት 11 እና 12 2014 በዋሽንግተን ዲሲ ይካሄዳል።

ቦታና ሰአቱን በቅርቡ እንገልፃለን።

በአውሮፓና በካናዳ መፅሃፉን ማከፋፈል የምትሹ በሚከተለው አድራሻ ፍላጎታችሁን ግለፁ።

Thursday, September 18, 2014

“የጀሚላ እናት” ጥቅምት 10 2014


“የጀሚላ እናት” ጥቅምት 10 2014 ገበያ ላይ ይውላል።

መፅሃፉን በሸጋ ሬስቶራንት ያገኙታል። አድራሻ፡

 

Shagga Restaurant

6040 Baltimore ave.

Hyattsville MD 20781

 

(“የስደተኛው ማስታወሻ” እና “የቡርቃ ዝምታ” በተጠቀሰው አድራሻ ይገኛሉ።)

Thursday, January 23, 2014

የሰለሙና ወጎች


ጊዜው ህዳር አጋማሽ ነበር - 2013

ረፋዱ ላይ ወደ ከረን የሚወስደውን መንገድ በመተው ወደ ዛግር አቅጣጫ ታጠፍን። ረጅም ጉዞ ስለሚጠብቀን ከወዲ ሓሬና ብዙ ወግ እንደማገኝ ርግጠኛ ነበርኩ። ከሚጠብቁኝ ወጎች መካከል፣ “የስደተኛው ማስታወሻ” ህትመት መቋረጥ፤ የጫልቱ ሚደቅሳ ግለ - ታሪክ ጉዳይ እና የመጪው ዘመን የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ የግድ የሚነሱ ነበሩ። ሆኖም እንደሚጠበቀው በቀጥታ ወደነዚህ ርእሰ ጉዳዮች አልገባንም። በቅድሚያ ቀላል ወጎችን ተጨዋወትን።

Monday, September 30, 2013

የእሬቻን በአል አከበርኩ!

 ቅዳሜ መስከረም 28, 2013 እዚህ አምስተርዳም ከተማ የእሬቻን በአል አከበርኩ። ከሶስት መቶ በላይ ሰዎች በአሉን ለማክበር መጥተው ነበር። “ያ! መሬሆ!” እያልን ወደ ውሃው ተጓዝን። ከዚያም ቢጫ አበቦች እና እርጥብ ቅጠል ውሃው ላይ አስቀመጥን። አብዛኛው የበአሉ ታዳሚ የኦሮሞን ባህላዊ ልብስ ለብሶ ነበር። ሴቶች እና ህፃናትም በብዛት ነበሩ። በአካባቢው የነበረ አንድ ሆላንዳዊ በመደነቅ አፉን ከፍቶ ትርኢቱን ይመለከት ነበር።